1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገና በዓል አከባበር በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2012

ላሊበላዎች በዓሉን በድምቀት የሚያከብሩት የየሱስ ክርስቶስ ልደት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱስ ላሊበላ ልደትም ጭምር በመሆኑ ነዉ።ድርብ በዓል።ላሊበላ ዉስጥ በዓሉን የሚያከብሩት ደግሞ የከተማይቱ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ የእምነቱ ተከታዮች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/3Vqj8
Äthiopien Charity-Aktion von EYES
ምስል DW/M. Hailesilassie

የገና በዓል ኃይማኖታዊ፣ ባሕላዊ ትርጓሜዉና ሥርዓቱ

የዩልያን (Julian) የቀን አቆጣጠር የሚከተለዉ የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ምዕመን ዛሬ 2012ኛዉን የየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ወይም ገናን አክብሮ ነዉ የዋለዉ።የኢትዮጵያ የክርስትና እምነት ተከታዮችም በዓሉን በተለያዩ ኃይማኖታዊና ባሕላዊ ሥርዓት እያከበሩት ነዉ።የበዓሉን አከባበር፣ኃይማኖታዊና ባሕላዊ ትርጓሜዉን፣ለችግረኞች የሚሰጠዉን ድጋፍና ርዳታን በተመለከተ ከአዲስ አበባ፣ከባሕርዳር፣ ከመቀሌና ከሐዋሳ የደረሱንን ዘገቦች እናሰማችኋለን።

ከአዲስ አበባ እንጀምር። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ያነጋገራቸዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሊቅ የበዓሉን ሐይማኖታዊና ባሕላዊ ፍቺ ዘርዘር አድርገዉ ያስረዳሉ።ሊቁ እንደሚሉት ከቅርብ ጊዜ ወዲሕ በተለይ በከተሞች አካባቢ የሚኖረዉ የክርስትና እምነት ተከታይ ገናን የሚያከብርበት ሥርዓት ከነበሩ ኃይማኖታዊና ባሕላዊ ሥርዓት ያፈነገጠ ነዉ።

የገና በዓል በየዓመቱ በድምቀት ከሚከባርባቸዉ አካባቢዎች አንዱ የላሊበላ ከተማ ነዉ።ላሊበላዎች በዓሉን በድምቀት የሚያከብሩት የየሱስ ክርስቶስ ልደት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱስ ላሊበላ ልደትም ጭምር በመሆኑ ነዉ።ድርብ በዓል።ላሊበላ ዉስጥ በዓሉን የሚያከብሩት ደግሞ የከተማይቱ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ የእምነቱ ተከታዮች ናቸዉ።

የባሕርዳሩ ወኪላችን ዓለምነዉ መኮንን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።ከባሕርዳር ሽቅብ ወደ ሰሜን ስናዳምጥ፣  EYES በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ ግብረ-ሰናይ ድርጅት መቀሌ ላይ ያደረገዉን በጎ ምግባር እንሰማለን።ለወትሮዉ ትምሕርትና ትምሕርት ነክ ለሆኑ ጉዳዮች ትኩረት የሚሰጠዉ ድርጅት ዛሬ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ መቀሌ ለሰፈሩና ለሚኖሩ ለተፈናቃዮችና ለአቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ አድርጓል።ዘጋቢያችን ሚሊዮን ኃይለስላሴ እንደሚለዉ EYES ምሳ ያበላቸዉ ችግረኞች ቁጥር ከአንድ ሺሕ ይበልጣል።

ከሰሜን መቀሌ ወደ ደቡብ እንዉረድ።ሐዋሳ።ከሐዋሳ በዓል አክባሪዎች አንዱና ቤተሰባቸዉ የዘንድሮ ገናን እንደ ወትሮዉ ከወዳጅ፣ዘመድ፣ ጎረቤት ጋር አላከበሩም።ሌላ ሥፍራ፣ ከሌሎች ጋር ማክበሩን ፈቀዱ።አቶ ተስፋዬ ፀጋዬ እና ቤተሰባቸዉ ምግብና መጠጥ ሲያዘጋጁ ሰነበቱ፣ ድንኳን ጣሉ፣ በዓሉን ጠገብ፣ዘና ብለዉ ማክበር የማይችሉ ደካሞችን ጋበዙ።አብረዉም ተቋደሱ።ወኪላችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ግብዣ ድግሱን ተከታትሎታል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ዓለምነዉ መኮንን

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ

መልካም በዓል

(ዝርዝር ዘገባዎቹን  ከየድምፅ ማዕቀፉ ማድመጥ ይቻላል።)

 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ