1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገበታ ለሀገር የወንጪ-ደንዲ ፕሮጀክት ተጀመረ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 11 2013

የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ-ደንዲ ኢኮ-ቱሪዝም ፕሮጀክት የግንባታ ሂደት ዛሬ በይፋ ተጀመረ፡፡በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ እንደሚሰራና የመጀመሪያው ምዕራፍ በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለለት ፕሮጀክቱ በአከባቢው የላቀ የጎብኚዎች መስዕብን እምርታ ያሳድጋል ነው የተባለው።

https://p.dw.com/p/3quXZ
Äthiopien Wanchi Ökotourismus
ምስል Seyoum Getu Hailu/DW

የወንጪ-ደንዲ ፕሮጀክት መጀመር


የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት አካል የሆነው የወንጪ-ደንዲ ኢኮ-ቱሪዝም ፕሮጀክት የግንባታ ሂደት ዛሬ በይፋ ተጀመረ፡፡ በሶስት ምዕራፎች ተከፍሎ እንደሚሰራና የመጀመሪያው ምዕራፍ በአንድ ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለለት ፕሮጀክቱ በአከባቢው የላቀ የጎብኚዎች መስዕብን እምርታ ያሳድጋል ነው የተባለው። የፕሮጀክቱ ኃላፊና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም በላይ በፕሮጀክቱ የሚጠቃለሉ በርካታ የቱሪስት መስዕብ ማዕከላት እንደሚገነቡበት ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት ጋር በስፍራው ተገኝተው የፕሮጀክቱ ስራ መጀመርን በገለጹበት በስነስርዓቱ ላይ ወንጪን የቱሪዝም ማዕከል የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው ጊዜ እውን ይሆናሉ ብለዋል፡፡
ስዩም ጌቱ
ታምራት ዲንሳ