የገሀዱ ዓለም ገጽ
እሑድ፣ መጋቢት 29 2011ማስታወቂያ
የፊልም ተዋናዩን ወይም ተዋናይቱን ገጽ በመቀየር በፊልሙ ታሪክ ላይ ሕይወት ይዘሩበታል፤ አዛውንት፣ የተጎዳ፣ የታመመ፣ እና ሌሎችም መሰል ገጸ ባህሪያትን አስመስሎ በማዘጋጀት ከፊልም ባለሙያዎች ጋር በጋራ ይሠራሉ፤ የፊልም የገጽ ቅብ ባለሙያዎች ማለትም (Makeup) አርቲስቶች።
በየፊልሙ የሚሳተፉትን ተዋንያን በገጽታም ሆነ በአካል ገጸ ባህሪውን መስለው ለመተወን እንዲችሉ የገጽ ቅብ ባለሙያ (Makeup Artist) ድርሻ የጎላ ነው ይሏቸዋል። ተዋናዩ በፊልሙ ደራሲ ከቀረጸው ገፀባህሪ ጋር ፍፁም እንዲመሳሰል በሚያደርጉት ጥረትም፤ የተመልካቹን ስሜት ልክ በገሀዱ ዓለም ያለ ያህል እንዲይዝ ያደርጋሉ።
በኢትዮጵያም በፊልሞቻችን በገጽ ቅብ ማለትም (Makeup) እድገት እየታየ መጥቷል ትላለች መሠረት መኮንን የፊልም ሜክአፕ ባለሙያ። ባሳለፍነው ሳምንት በተደረገው የጉማ ፊልም ሽልማት በሲመት ፊልም የገጽ ቅብ አሸናፊ ሆናለች።
ነጃት ኢብራሂም
ሸዋዮ ለገሰ