1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጅቡቲ ድሬዳዋ መስመር ተከፈተ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 22 2013

መስመሩን የዘጉት በአፋርና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰዉን ግጭት መንግሥት እንዲያስቆም የሚጠይቁ የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ነበሩ።በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን እንዳስታወቀዉ የመኪናና የባቡር መንገዶቹ ከትናንት ጀምረዉ ተከፍተዋል

https://p.dw.com/p/3yHbY
Stadt Dire Dawa in Äthiopien
ምስል Hailegzi Mehari

«ሾፌሮች ግን ገንዘብ እንዲከፍሉ ይገደዳሉ» ማሕበር

ለሁለት ቀናት ተዘግቶ የነበረዉ የድሬዳዋ-ጅቡቲ የመኪናና የባቡር መስመር ዳግም አገልግሎት  መስጠት ጀመረ።መስመሩን የዘጉት በአፋርና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ድንበር አካባቢ የተቀሰቀሰዉን ግጭት መንግሥት እንዲያስቆም የሚጠይቁ የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ነበሩ።በሶማሌ ክልል የሲቲ ዞን እንዳስታወቀዉ የመኪናና የባቡር መንገዶቹ ከትናንት ጀምረዉ ተከፍተዋል።ይሁንና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማበር፣ አንዳድ ቦታዎች የየአካባቢዉ ነዋሪዎች መንገድ እየዘጉ ለማለፍ የሚፈልጉ ሾፌሮችን ገንዘብ እንዲከፍሉ እያስገደዷቸዉ መሆኑን አስታዉቋል።

መሳይ ተክሉ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ