አነጋጋሪዉ የጀርመን የመከላከያ ሚንስትር ከፓርቲ ሀላፊነት መልቀቅ
ማክሰኞ፣ የካቲት 3 2012ማስታወቂያ
የጀርመን የመከላከያ ሚንስትር አነግሬት ክራምፕ ካረንባወር ከፖለቲካ ኃላፊነታቸዉ መልቀቃቸዉን በትናንትናዉ ዕለት አስታዉቀዋል። የክርስቲያን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር የነበሩት ካረንባወር መራሂተ-መንግሥት አንጌላ ሜርከልን ይተካሉ ተብሎ ሲጠበቁ ትናንት የወሰዱት ድንገተኛ ርምጃ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ሚኒስትሯ አዲሲቱን የአውሮጳ ሕብረት ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎንዴርላየንን ተክተዉ በጎርጎሮሳዊው ሐምሌ 2019 የጀርመን መከላከያ ሚንስትርነቱን ሥልጣን የያዙ ሲሆን ከክርስቲያን ዴሞክራቲክ ፓርቲ መሪነታቸውም ሆነ ከቀጣይ እጩ መራሂተ መንግሥትነታቸው ራሳቸዉን ማግለላቸዉ ሜርከልን ጨምሮ ብዙዎችን አስደንግጧል። ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ወገኖች የፖለቲከኛዋ ርምጃ ከፓርቲያቸው ፖለቲካዊ ጨዋታ ጋር ይገናኛል ባይ ናቸው።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ፀሀይ ጫኔ
ሽዋዬ ለገሰ