1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የጀርመን የእንቅስቃሴ ዕገዳ ማሻሻያ

ሐሙስ፣ የካቲት 25 2013

የ16ቱ ክፍለ-ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ትናንት ከመራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር ባደረጉት ዉይይት ተዘግተዉ ከነበሩ ተቋማትና ድርጅቶች መካከል መፅሐፍት፣ አበባና የመናፈሻ አትክልት መሸጪያ መደብሮች እንዲከፈቱ ወስነዋል።

https://p.dw.com/p/3qDe7
Impfgipfel im Bundeskanzleramt
ምስል Steffen Kugler/Bundesregierung/dpa/picture alliance

የጀርመን የመንቀሳቀስ እገዳ መሻሻል

  የጀርመን መንግሥት የኮሮና ተሕዋሲ ስርጭትን ለመግታት በሰዎች ዝዉዉር፣ ግንኙነትና እንቅስቃሴ ላይ የጣለዉ ዕገዳ በመጠኑ ተሻሽሏል።የ16ቱ ክፍለ-ግዛቶች አስተዳዳሪዎች ትናንት ከመራሂተ-መንግስት አንጌላ ሜርክል ጋር ባደረጉት ዉይይት ተዘግተዉ ከነበሩ ተቋማትና ድርጅቶች መካከል መፅሐፍት፣ አበባና የመናፈሻ አትክልት መሸጪያ መደብሮች እንዲከፈቱ ወስነዋል።የየክፍለ-ግዛቱ አስተዳደር በየአካባቢያቸዉ በየሳምንቱ በኮሮና ተሕዋሲ የሚያዘዉን ሰዉ ቁጥር እየተከታተሉ ሌሎች ማሻሻዎችን እንዲያደርጉም ተሰብሳቢዎቹ ተስማምተዋል።ከማሻሻዉ ዉጪ ባለፈዉ ታሕሳስ መጀመሪያ የተጣለዉ አጠቃላይ እገዳ ግን  እስከ መጋቢት ማብቂያ ድረስ ይቀጥላል።

ይልማ ኃይለሚካኤል 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ