1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን እና የናሚቢያ ድርድር መቋጫ ሊያገኝ ነዉ

ዓርብ፣ ሰኔ 12 2012

ጀርመን እና  ናሚቢያ በቅኝ ግዛት ዘመን ናሚቢያ ዉስጥ ለተፈጸሙት ወንጀሎች የጀመሩት ድርድር በሚቀጥለዉ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ። ሁለቱ ሃገራት በቅኝ ግዛት ዘመን የነበረዉን ወንጀል ይቅርታ ለመጠየቅ ብሎም ካሳ ለመክፈል የሚያደርጉትን ድርድር ከጀመሩ ዓመታት ማስቆጠሩ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/3e3xb
Deutsche Kolonialbeamte in Lome Togo
ምስል picture-alliance/akg-images

ጀርመን እና  ናሚቢያ በቅኝ ግዛት ዘመን ናሚቢያ ዉስጥ ለተፈጸሙት ወንጀሎች የጀመሩት ድርድር በሚቀጥለዉ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለፀ። ሁለቱ ሃገራት በቅኝ ግዛት ዘመን የነበረዉን ወንጀል ይቅርታ ለመጠየቅ ብሎም ካሳ ለመክፈል የሚያደርጉትን ድርድር ከጀመሩ ዓመታት ማስቆጠሩ ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ ጀርመንን ወክለዉ የሚደራደሩት ቡድን መሪ ሩፕሬሽት ፖሌንዝ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ድርድሩ በሚቀጥለዉ የጎርጎረሳዉያን 2021 ዓመት በጀርመን የምክር ቤት ምርጫ ከመደረጉ በፌት ይጠናቀቃል ብለዉ እንደሚያምኑ  ተናግረዋል። ጀርመን በሚቀጥለዉ ዓመት ቢዘገይ እስከ ጥቅምት ወር የምክር ቤት ምርጫን እንደምታካሂድ የወጣዉ መዘርዝር ያሳያል።  ከጎርጎረሳዉያኑ 1904 እስከ 1908 ዓመት በዝያን ወቅት ጀርመን - ደቡብ ምዕራብ አፍሪቃ ተብላ በምትጠራዉ በዛሬዋ ናሚቢያ የጀርመን ቅኝ ገዥ ጦር  በአስር ሺህ የሚቆጠሩ  የናሚቢያ ተወላጆችን በተለይ የሄሬሮ እና ናማ ጎሳዎችን መግደላቸዉ በታሪክ ተፅፎአል።  በጎርጎረሳዉያኑ 2017 ዓ. ም  በዝያን ጊዜዉ   የጀርመን ቅኝ ገዢ ጦር በናሚቢያ ሕዝብ ላይ ለተፈፀመዉ  ጭፍጨፋ የጀርመን መንግሥት ለተበዳይ ወገኖች ካሳ እንዲከፍል ሲሉ የሄሬሮ እና የናማ ጎሳ ተወካዮች በኒው ዮርክ ዩኤስ አሜሪካ ክስ መመስረታቸው የሚታወስ ነዉ።

አዜብ ታደሰ 

ነጋሽ መሐመድ