1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጉድኝት

ሰኞ፣ ጥቅምት 19 2011

የአዉሮጳ ጉብኝታቸዉን ዛሬ ከፓሪስ ፈረንሳይ የጀመሩት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አሕመድ ነገ ጀርመን በርሊን ከተማ ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ በጀርመን ጉብኝታቸዉ በርሊን ዉስጥ ከጀርመን ባለሥልጣናት እና ከባለሃብቶች ጋር ይወያያሉ።

https://p.dw.com/p/37Lq1
Deutschland | Skyline Berlin | Nikolaiviertel mit Fernsehturm
ምስል picture-alliance/R. Schlesinger

የጀርመን ኢትዮጵያ ታሪካዊ ጉድኝት

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በበርሊን ከአንድ ቀን ጉብኝት በኋላ ወደ ፍራንክፈርት ከተማ ተጉዘዉ ከመላዉ አዉሮጳ ለሚሰበሰቡ ኢትዮጵያዉያን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ስለሚያራምዱት የታህድሶ ለዉጥ ማብራርያና ገለጻ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። የዶ/ር  ዐብይ አህመድ ጉብኝት ረጅም ዘመን ያስቆጠረዉን የኢትዮጵያና የጀርመንን ግንኙነት ይበልጥ ያጠናክራልም ተብሎአል። ስለሁለቱ ሃገራት ግንኙነት የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ከታሪክ ምሁሩ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘዉዴን አነጋግሮአል። ሙሉ ቅንብሩን ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ፤

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ