1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሁለት ሆስፒታሎች ያደረገው ድጋፍ ተደረገ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 29 2012

የጀርመን ስጋ ደዌ እና ቲቢ እርዳታ ማህበር ለቢሲዲሞ እና ሻሸመኔ ሆስፒታሎች ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ያግዛሉ ያላቸውን የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ ። ማህበሩ በተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መሰል ድጋፍ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3dLW4
Türkei Istanbul | Moschee wird zur Hilfsstation für Betroffene der Coronakrise
ምስል DW/S. Rahim

የጀርመን ስጋ ደዌ እና ቲቢ እርዳታ ማህበር

የጀርመን ስጋ ደዌ እና ቲቢ እርዳታ ማህበር ለቢሲዲሞ እና ሻሸመኔ ሆስፒታሎች ለኮሮና ቫይረስ መከላከል ያግዛሉ ያላቸውን የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ ። ማህበሩ በተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መሰል ድጋፍ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።የጀርመን ስጋ ደዌ እና ቲቢ እርዳታ ማህበር የምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ አቶ አህመድ መሀመድ ለDW በስልክ በሰጡት መግለጫ ማህበሩ ለቢሲዲሞ እና ሻሸመኔ ሆስፒታሎች ኮሮናን ለመከላከል የሚያግዙ የህክምና ቁሳቁሶች እና በወረርሽኙ ሳቢያ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎችም የምግብ ድጋፍ መስጥቱን ተናግረዋል።
ማህበሩ ቀደም ሲልም የተለያዩ ስራዎች ሲሰራ እንደነበር የጠቆሙት ኃላፊው ለኮቪድ 19 ችግር የበኩሉን ድጋፍ ለመስጠት በጀመረው እንቅስቃሴ የተለያዩ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት እና የመንም ለዚሁ አካባቢ ትቀርባለች በሚል መሰል ስራ ለመስራት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።ትናንት ድጋፍ የተደረገለት የቢሲዲሞ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ አቶ ጫላ አብራሂም የቢሲዲሞ አጠቃላይ ሆስፒታል ምስረታ ጀምሮ ያቋቋመ እና በየጊዜውም ለሆስፒታሉ የተለያዩ ድጋፎችን የሚያደርግ ነው ያሉት የጀርመን ስጋ ደዌ እና ቲቢ ማህበር አሁን የሰጠው ድጋፍ ጠቃሚ መሆኑን ተናግረዋል ።ሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ስጋትን ለመከላከል ግንዛቤን ከማስጨበጥ ጀምሮ በተቋሙ ለይቶ ማቆያ በማዘጋጀት እየሰራ መሆኑን አቶ ጫላ አስረድተዋል ።የጀርመን ስጋ ደዌ እና ቲቢ እርዳታ ማህበር በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ አለም ሀገራት እየሰራ መሆኑን ያስታወቁት የማህበሩ ምስራቅ አፍሪካ ተጠሪ አቶ አህመድ በስጋ ደዌ እና ቲቢ መከላከል ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል። ማህበሩ በ1957 ዓ.ም ተመስርቶ የመጀመሪያ ስራውን በ1958 ዓ.ም ኢትዮጵያ ውስጥ መጀመሩን ኃላፊው የሰጡት መረጃ ያመለክታል።

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ