የጀርመናውያኑ ፍራቻ ከምን ይመነጫል?
ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2011ማስታወቂያ
ጀርመናውያን ከሚያሳስቧቸው አበይት ጉዳዮች መካከል ወደ አገሪቱ የሚነጉዱ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ስደተኞች እና ፍላጎቶቻቸው ይገኝበታል። በጀርመን በተሰራ አንድ ጥናት መሠረት በርካታ ዜጎች አገሪቱ ከጎርጎሮሳዊው 2015 ዓ.ም. ወዲህ የበረታውን የስደት ቀውስ መቋቋም አትችልም የሚል ሥጋት ተጭኗቸዋል። ምጣኔ-ሐብታዊ ውድቀት፣ ሽብርተኝነት እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሚከተሉት የፖለቲካ ፍልስፍና እና በዓለም ላይ የሚያሳድሩት ጫና በጀርመናውያን ዜጎች ዘንድ ፍራቻ ካሳደሩ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል።
በዛሬው የአውሮፓ እና ጀርመን መሰናዶ ይልማ ኃይለሚካኤል ጀርመናውያኑን የሚያሳስቧቸውን ጉዳዮች ይዳስሳል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
እሸቴ በቀለ