የዶ/ር ደብረጽዮን መግለጫና የድሮን ጥቃት በመቀሌ
ሰኞ፣ ኅዳር 27 2014ማስታወቂያ
«የትግራይ ታጣቂ ኃይሎች» ከዚህ ቀደም ይዘዋቸው የነበሩ አንዳንድ አካባቢዎችን ለቀው የወጡት ከማንኛውም ጫና ውጭ በራስ ተነሳሽነት መሆኑን ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል አስታወቁ። መንግሥት አሸባሪ የሚለው የህወሓት ሊቀ መንበርና የትግራይ ክልል አስተዳዳሪ ዶክተር ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል ትናንት በሰጡት መግለጫ የህወሓት ታጣቂዎች አካባቢዎቹን የለቀቁት «ስልታዊ ለውጦችን» በማድረግ ነው ብለዋል።በሌላ በኩል ትናንት መቀሌ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት ሁለት መኖሪያ ቤቶች ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዶቼ ቬለ ወኪል ከመቀሌ ዘግቧል።
ሚሊዮን ኃይለ ሥላሴ
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ