የድሬዳዋው የመሬት ወረራ
ቅዳሜ፣ መጋቢት 14 2011ማስታወቂያ
ድሬዳዋ ውስጥ በሚገኘው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተ ክርስቲያን ሰሞኑን በተፈፀመ የመሬት ወረራ የተጠረጠሩ ሰዎች መያዛቸውን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታውቋል። ፖሊስ በወቅቱ በቤተክርስቲያኗ ላይ የተካሄደውን የመሬት ወረራን ባለመከላከል፣ ተያይዞ ለተከሰተው ችግርም ፈጥኖ መፍትሄ ባለመስጠት ቅሬታ ቀርቦበታል። የድሬዳዋ ፖሊስም በወቅቱ ህግን ለማስፈጸም በሚፈለገው መጠን አለመሰራቱን ለDW አስታውቋል። የድሬዳዋ አስተዳደር በበኩሉ ከመሬት ወረራው እና ህገ ወጥ ከሚባሉ ግንባታዎች ጋር ለተያያዙ ችግሮች መፍትሄ አስቀምጫለሁ ይላል። መሳይ ተክሉ ከድሬዳዋ ዘገባ ልኮልናል።
መሳይ ተክሉ
ኂሩት መለሰ
እሸቴ በቀለ