የድሬዳዋው ሲሳይ ዘለገሀሬ የግጥም ስራዎች
እሑድ፣ ታኅሣሥ 10 2014ማስታወቂያ
ድሬደዋ ካፈራቻቸው የጥበብ ሰዎች በቀዳሚነት ስሙ የሚነሳው ገጣሚ ሲሳይ ዘለገሀሬ ከግጥም ስራዎቹ ያቀረበልን አጭር ስንኝ ነበር። የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅታችን ከድሬደዋው ገጣሚ ጋር ያደረግነውን ጥቂት ቆይታ ይዳስሳል።
"ለፍቅራችሁ" ገጣሚ ሲሳይ ከስምንት አመት በፊት ያሳተመው የግጥም መፅሀፍ ርዕስ ነበር። የዚያን ጊዜው መፅሀፍ ከብዙዎች አስተዋውቆኛል የሚለው ሲሳይ ከዚያ በኃላ ግን መፅሀፍ ማሳተም ሀሳቡ ቢኖረውም በተለያየ ምክንያት ማሳተም አለመቻሉን አጫውቶናል።
ከነፍስ የግጥም ስራዎች ባለፈ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚፅፋቸውን ግጥሞቹን በመድረክ በማቅረብ የብዙዎችን ቀልብ በመሳብ ይታወቃል - ሲሳይ ። ከእነዚህ መካከል እርሱም የሚያስታውሰውን "መንዳት እና መምራት" ተጠቃሽ ነው።
ሲሳይ ተወልዶ ባደገባት ድሬደዋ ስመ ጥር ከሆኑ የጥበብ ፈርጦች አንዱ ሆኖ ከተማዋን በአንድም በሌላ መልኩ በስራዎቹ ሲያስተዋውቃት ኖሯል ። እሷ ግን ያን ያክል ውለታውን እየከፈለችው ባለመሆኑ ተስፋ ወደ መቁረጡ መሄዱን ተናግሯል።
መሳይ ተክሉ
ታምራት ዲንሳ