1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት አቋቋመ

ረቡዕ፣ መስከረም 19 2014

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መስራች ጉባዔው አቶ ከድር ጁሀርን ከንቲባ አድርጎ ሾመ። የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ጉባኤ ዛሬ አከናውኗል። በጉባዔው ወ/ሮ ፈትያ አደም የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ለቀጣይ አምስት አመት እንዲያገለግሉ ተሹመዋል።

https://p.dw.com/p/4131I
Äthiopien Bürgermeister Dire Dawa Kedir Juhar
ምስል Mesay Tekelu/DW

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት አቋቋመ

የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መስራች ጉባዔው አቶ ከድር ጁሀርን ከንቲባ አድርጎ ሾመ። የድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር አዲስ መንግስት መመስረት የሚያስችለውን ጉባኤ ዛሬ አከናውኗል። በጉባዔው ወ/ሮ ፈትያ አደም የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ሆነው ለቀጣይ አምስት አመት እንዲያገለግሉ ተሹመዋል። አንድ መቶ ሰማንያ ዘጠኝ አባላት ያለውን የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ወ/ሮ ከሪማ አሊ በምክትል አፈ ጉባዔነት እንዱመሩ ተሹመዋል። የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው 3ኛ የስራ ዘመን የመጀመሪያ ዓመት 49ኛ  ጉባዔው ለቀጣይ አምስት አመት የሚያገለግሉ የካቢኔ አባላትን ይፋ አድርጓል።

መሳይ ተክሉ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ