1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬደዋ ረቂቅ ቻርተር አዋጅ

ዓርብ፣ ሐምሌ 8 2014

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመበትን ቻርተር ለማሻሻል የሚያስችል ረቂቅ ቻርተር አዋጅ ይፋ አደረገ። በአስተዳደሩ የሚገኙ ሠላሳ ስምንት የገጠር ቀበሌዎችን እውቅና ሰጥቶ ያላካተተው የቀድሞው የከተማዋ ማቋቋምያ ቻርተር በ1996 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ነበር።

https://p.dw.com/p/4EChj
Äthiopien | Sebsebe Mekonnen | Berater des Bürgermeisters
ምስል Messay Teklu/DW

ረቂቅ አዋጁ በአስተዳደሩ ሦስት ቋንቋዎች የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ሀሳብ ተካቶበታል።

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የተቋቋመበትን ቻርተር ለማሻሻል የሚያስችል ረቂቅ ቻርተር አዋጅ ይፋ አደረገ። በአስተዳደሩ የሚገኙ ሠላሳ ስምንት የገጠር ቀበሌዎችን እውቅና ሰጥቶ ያላካተተው የቀድሞው የከተማዋ ማቋቋምያ ቻርተር በ1996 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ ነበር።

Äthiopien | Öffentliche Diskussion in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu/DW

የከተማ አስተዳደሩ የተቋቋመበትን ቻርተር ለማሻሻል በተዘጋጀው አዲስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከአስተዳደሩ ነዋሪ ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሂዷል። በረቂቅ ቻርተር አዋጅ ዝግጅቱ ተሳታፊ የሆኑት የህግ ባለሞያው አቶ ሰብስቤ መኮንን ቀደም ሲል በነበረው ቻርተር የህዝብ ቅሬታ ያሳድሩ በነበሩ  የህግ ማውጣት ፣ ማስፈፀም እና መተርጎም ሂደቶች ላይ ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል ።

ለከተማዋ እድገት ማነቆ ተደርጎ ለዓመታት ሲነሳ የነበረው ከከተማዋ የሚመነጭ የገቢ ክፍፍል ጉዳይም በረቂቅ ቻርተሩ እንዲታይ መደረጉን አቶ ሰብስቤ አስረድተዋል። በረቂቅ ቻርተሩ እውቅና ተነፍገው የቆዩትን የገጠር ቀበሌዎች አካቶ በርእሰ መስተዳድር እንዲመራ እንዲሁም የመስተዳድሩን ፖሊስ ኮምሽን ተጠሪነት ወደ አስተዳደሩ እንዲመለስ የሚያደርግ ሀሳብም በረቂቁ መካተቱን አቶ ሰብስቤ ገልፀዋል።

Äthiopien | Öffentliche Diskussion in Dire Dawa
ምስል Messay Teklu/DW

ከህዝብ ተወካዮች ጋር በተደረገ ውይይት መድረክ የቀረበው ረቂቅ ቻርተር አዋጅ የረዥም ጊዜ ጥያቄን የመለሰ መሆኑ ተነስቷል። በኢፌድሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ መፅደቅ በሚጠበቅበት ረቂቅ ቻርተር አዋጅ በአስተዳደሩ ሶስት ቋንቋዎች የስራ ቋንቋ እንዲሆኑ ሀሳብ ተካቷል። ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ ውይይት ተደርጎበት ለህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት እንደሚላክ ለማወቅ ተችሏል ።

መሳይ ተክሉ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ