1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድምጻዊት መርጊቱ ወርቅነህ «ኦቦምቦሌቲ » የሙዚቃ ሕይወት

እሑድ፣ ኅዳር 5 2014

ትውልድ እና ዕድገቷ አምቦ ከተማ ነው። ልክ እንደ አብዛኛው የሙዚቃ ሰው ለሚዚቃ መፈጠርዋን ከአቻ ጓደኞቿ እና ለእርስዋ ቅርበት ካላቸው ሰዎች  ተረድታ ነው የሙዚቃውን ዓለም የተቀላቀለችው ፤ ድምጻዊት መርጊቱ  ወርቅነህ።

https://p.dw.com/p/42ym4
Artist Megitu Workineh
ምስል Tamirat Dinssa/DW

የአርቲስት መርጊቱ ወርቅነህ የሙዚቃ ስራዎች

ትውልድ እና ዕድገቷ አምቦ ከተማ ነው። ልክ እንደ አብዛኛው የሙዚቃ ሰው ለሚዚቃ መፈጠርዋን ከአቻ ጓደኞቿ እና ለእርስዋ ቅርበት ካላቸው ሰዎች  ተረድታ ነው የሙዚቃውን ዓለም የተቀላቀለችው ፤ ድምጻዊት መርጊቱ  ወርቅነህ። ጤና ይስጥልን አድማጮቻችን የዛሬ የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን በአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎቿ በጥቂት ስራዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘችው እና ተስፈኛዋ ሙዚቀኛ መርጊቱ ወርቅነህ ናት መልካም ቆይታ

Artist Megitu Workineh
ምስል Tamirat Dinssa/DW

አመ ዬሮን የተሰኘውን ነጠላ ዜማዋን ከሰራች በኋላ መርጊቱ ለሁለት ዓመታት ያህል ከሙዚቃው መድረክ ገለል ብላ ቆይታለች ። ምክንያቷ ደግሞ ከስምንት ዓመታት ፍቅረኛዋ ትዳር መስርታ የልጅ እናት በመሆኗ እንደነበር ትናገራለች ።በመጀመርያው የሙዚቃ ስራዋ ተወዳጅነትን የማትረፏን ያህል መሰወሯ ካነጋገረ በኋላ መርጊቱ በሌላ አዲስ የነጠላ ሙዚቃ ተከስታለች። ኦቦምቦሌቲ ደግሞ የሙዚቃው መጠርያ ነው። ኦቦምቦሌቲ ልክ እንደመጀመርያው ነጠላ ዜማ ሁሉ ከፍተኛ ተቀባይነት አስገኝቶላታል።

Artist Megitu Workineh
ምስል Tamirat Dinssa/DW

ድምጻዊት መርጊቱ በቀጣይ ሙሉ የሙዚቃ አልበም ሰርታ ለአድማጭ ተመልካች የማቅረብ ትልቅ ዕቅድ እንዳላትም ነግራናለች። እንግዲህ አድማጮቻችን ከድምጻዊት መርጊቱ ወርቅነህ ጋር የነበረው የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅታችን ይህን ይመስል ነበር ስትከታተሉን ለነበራችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ በያላችሁበት ጤና ይስጥልን።

ታምራት ዲንሳ