1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዳንር እና የጃዊ ተፈናቃዮች ሮሮ

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 8 2012

የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ጽ/ቤት ከሐምሌ 2011 አንስቶ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች አዋቂዎችን ጨምሮ 14 ህጻናት በወባ እና የተለያዩ በሽታዎች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡በጥቅምት ወር  የሚቀርበው እርዳታ ዘግይቶ እንደነበር የተናገሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በፓዌ ወረዳ ከውሀ እጥረት ውጭ ወቅቱን ጠብቆ ዕርዳታ እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3V0gz
Äthiopien Assosa | Tarekegn Tesisa - Leiter des Krisenmanagement Benishangul Gumuz
ምስል DW/N. Dessalegn

የጃዊ ተፈናቃዮች ሮሮ

ባለፈው ዓመት በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል፣ኦሮሚያ እና አማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች በነበረው የጸጥታ ችግር ከ92ሺ በላይ ዜጎች መፈናቀላቸውን የቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት የስራ አመራር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡ ከነዚህም መካከል 80ሺ የሚደርሱ ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞ መኖሪያቸው የተመለሱ ሲሆን ከስድስት ወራት በፊት ከመተከል ዞን የተለያዩ አካባቢዎች እና ጃዊ የተፈናቀሉ ከ10ሺ በላይ ዜጎች ደግሞ በግልገል በለስ፣ፓዌ፣ዳንጉር እና ማንደራ ተጠልው ይገኛሉ፡፡ በዚው አካባቢ በነበረው ግጭት ተፈናቅለው በግልገል በለስ ከተማና ፓዌ መንደር ተጠጥልው የሚገኙ ያነጋገርኳቸው አራት ተፈናቃዮች ተገቢው እርዳታ እያገኘን አይደለም ብለዋል፡፡

ከዳንጉር ተፈናቀለው በፓዊ መኖር ከጀመሩ ሰባት ወራትን እንደሆናቸው የተናገሩት አቶ ብርሀኑ ሊበን የእለት ተዕለት ኑሮአቸውን ለመምራት የሚያስችላቸውን ድጋፍ በመንግስት በኩል እያገኘን አይደለም ብለዋል፡፡ በወር 15ኪሎ የሚሆን የዕህል እርዳታ ብቻ እንደሚደርሳቸው ገልጸዋል፡፡  

Äthiopien Assosa | Schild des Krisenmanagement Büro für Benishangul Gumuz
ምስል DW/N. Dessalegn

ሌላው በሚዚያ 2011 ዓ.ም በጃዊ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ተፈናቅለው በግልገል በለስ ከተማ የሚገኙ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ተፈናቃይ በተመሳሳይ በመንግስት በኩል የሚደረጉ ድጋፎች በቂ አለመሆናቸውን ይናገራሉ፡፡  በግልገለበለስ ቻይና ካምፕ የተባለ ቦታ የሚኖሩት እኚሁ ቅሬታ አቅራቢ በጤና ችግር ምክንያት ስድስት የሚደርሱ ህጻናት መሞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽ/ቤት በበኩሉ በክልሉ እና ከከልሉ ውጭ ተፈናቅለው በተለያዩ ስፋራዎች ለሚገኙ ዜጎች እርዳታ ለማዳረስ በአሁኑ ወቅት በመተከል ዞን አራት ወረዳዎች ላይ እገዛ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡ የጽ/ቤቱ ሓላፊ አቶ ታረቀኝ ተሲሳ እንዳሉት ከመተከል ዞን እና ከጃዊ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚቀርበው እርዳታ በጥቅምት ወር ዘግይቶ የነበረ ሲሆን ባሁነ ጊዜ በየወሩ እርዳታ እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡  ከባለፈው ሐምሌ 2011 ዓ.ም አንስቶ በወባና የተለያዩ በሽተዎች አዋቂዎችን ጨምሮ 14 ህጻናት መሞታውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎችን በዘላቂነት ለማቋቋም የቤት ግንባታ በጃዊ እየተከናወነ ነው ያሉት ኃላፊው በጉባና ዳንገር የገጠር ቀቤሌዎች ደግሞ በመንገድ ችግር ምክንያት ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ መስራት እንዳልተቻለ ገልጸዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ