1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ በሙስና መጠርጠር

ቅዳሜ፣ ሰኔ 4 2014

ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎዛ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀልን አሰመልክቶ በፓርቲያቸው የአፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረንስ (ANC) እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን ፊት ቀርበው ምላሽ ሊሰጡ ነው። ፕሬዚደንቱ ምላሽ የሚሰጡት የቀድሞ የስለላ ዳይሬክተር አርተር ፍሬዘር ባለፈው ሳምንት የሙስና ቅሌት ዙሪያ የዘረፋ ውንጀላ ካቀረቡባቸው በኋላ ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/4CZBZ
Südafrika I Cyril Ramaphos I Untersuchung zu Korruptionsvorwürfen
ምስል Rodger Bosch/AFP

የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ እና ፓርቲያቸው አጣብቂን ውስጥ ናቸው

ወደ ተከታዩ ርዕሰ ጉዳያችን ስናልፍ በአፍሪቃ ከሰሞኑ አበይት የመነጋገሪያ ጉዳዮች ከነበሩት ውስጥ የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዣቅሌት እና ፓርቲያቸው የገጠመውን ፈተና ይመለከታል። 
ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎዛ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀልን አሰመልክቶ  በፓርቲያቸው የአፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረንስ (ANC)  እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን ፊት ቀርበው ምላሽ ሊሰጡ ነው። 
 የራማፎዛ የሙስና ቅሌት የተሰማው የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃ የስለላ ዳይሬክተር አርተር ፍሬዘር ባለፈው ሳምንት ፕሬዚዳንቱ በተጠረጠሩበት የሙስና ቅሌት ዙሪያ ሌላ የዘረፋ ውንጀላ ካቀረቡባቸው  በኋላ ነው ተብሏል። 
አርተር አገኘሁት ባሉት እና ለሀገሪቱ ፖሊስ አሹልከው በሰጡት መረጃ መሰረት ዘራፊዎች በሰሜናዊ ሊምፖፖ ግዛት ወደሚገኝ የራማፎዛ የእንስሳት እርባታ ስፍራ በማቅናት ዕቃ ውስጥ ተደብቆ የነበረ አራት ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ ማግኘታቸው ተገልጿል። 
ነገር ግን ከአፍታ ጊዜ በኋላ ገንዘቡን ወስደዋል የተባሉ ወንጀለኞች በቁጥጥር ስር የዋሉ ቢሆንም ስለ ገንዘቡ አንዳች መረጃ እንዳያወጡ ገንዘብ ተከፍሏቸው ዝም እንዲሉ መደረጋቸውን የቀድሞ የስለላ ሃላፊው ማጋለጣቸው ነው የተነገረው።
ይህንኑ ተከትሎም አርተር ራማፎዛ በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ፣ የሰዎች ዕገታ እና የሙስን ተግባራት ላይ መሰማራታቸውን አረጋግጠናል ሲሉ አጋልጠዋቸዋል። 
ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ አዲሱ ውንጀላ ከቀረበባቸው በኋላ ግን ማስተባበያ ሰጥተዋል ። በእርሻ ስፍራ ተገኘ የተባለው ገንዘብም ቢሆን የግላቸው እንጂ የሕዝብ ገንዘብ ላለመሆኑ ምላሽ መስጠታቸው ተደምጧል። ባለፈው እሁድ በሰጡት ቃላቸውም የእንስሳቱ ንግድ በባንክ የገንዘብ ዝውውር እና በካሽ የእጅ በእጅ ሽያጭ የሚከናወን ነው ሲሉ ራሳቸውን ተከላክለዋል። 
«እኔ በእንስሳት እርባታ እና ንግድ ስራ ላይ የተሰማራሁ ሰዉ ነኝ፤ እንስሳትን እገዛለሁ ደግሞም እሸጣለሁ፤ ይህ ደግሞ ግልጽ የንግድ ልውውጥ  ነው፤ » በማለት ለቀረበባቸው ውንጀላ ምላሻቸውን ሰጥተዋል። 
በስልጣን ላይ እያሉ የሙስና ቅሌት ክስ የቀረበባቸው ፕሬዚዳንት ራማፎዛ  በቀድሞው የስለላ ሃላፊ የቀረበባቸው ክስ በበርካቶች ዘንድ እንደ አዲስ መነጋገሪያ ሆነው ብቅ እንዲሉ አድርጓቸዋል። የሀገሪቱን ፖለቲካ በቅርበት የሚከታተሉ እና ትንታኔ የሚሰጡ ሰዎችም በአዲሱ ውንጀላ ከመልስ ይልቅ በጥያቄዎች የተሞላ ነው ሲሉ ሃሳባቸውን ያጋራሉ ። 
ከሃገሪቱ ታዋቂ የፖለቲካ ተንታኞች መካከል አንዱ የሆኑት ሉኮና ምንጉኒ ይህንኑ ሃሳብ አጠናክረው በሰነዘሩት አስተያየታቸው በርግጥ ጉዳዩ ከተሰማ በኋላ በፕሬዚዳንቱ ላይ በርካታ ጥያቆዎች የሚያስነሱ ሆኖ መገኘቱን ይገልጻሉ። በእርግጥ የፕሬዚደንቱ «ገንዘቡ ህጋዊ » ነው ምላሽ ህጋዊነቱ ተጣርቶ መታወቅ ይገባዋል ባይም ናቸው። ይህንኑ በተመለከተ በማህበራዊ መገናኛ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክታቸው እንዲህ ሲሉ ይጠይቃሉ።
« ግብይት ነበረ፣ ግብይት እስካለ ድረስ ደ,ግሞ ገቢም ይኖራል፤ ለመሆኑ ፕሬዚደንቱ ገቢያቸውን በአግባቡ አሳውቀው ግብር ከፍለውበታል ወይ ?» ቀጠል አድርገው ባሰፈሩት መልዕክታቸውም « ነው ወይስ ሽፋን ነበረው ?» ጥያቄዎች ጥያቄን አስከትለው እንደሚሄዱ ያሳዩ ሃሳቦች ከዚህም ከዚያም እየተደመጡ ነው። የማህበራዊ ሚዲያው በዚህ ረገድ በርካታ አወዛጋቢ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ የተገደደበት አጋጣሚም አስተናግዷል። 
በደቡብ አፍሪቃ የፋይናንስ ስረዓት ህግ መሰረት ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት ገንዘብ የሚያስተላልፍበትን ሂደት ገድቧል። 
በዚሁ ሙስና እና ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን ለመግታት ስራ ላይ የዋለው ህግ ከ1,520 ዩሮ በላይ የገንዘብ ክፍያዎች ወይም ደረሰኞች ወደ የሀገሪቱ የፋይናንስ ስረዓት መከታተያ ማዕከል ሪፖርት እንዲያደርጉ ይጠይቃል። 
ለመሆኑ የሰሞንኛው በፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ ላይ እየተናፈ,ሰ ያለው የሙስና ወንጀል በቀጣይ ፖለቲካዊ ሚናቸው ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድር ይሆን ? በዚህ ረገድ በፖለቲካ ተንታኞችም ሆነ ጉዳዩን በቅርበት በሚከታተሉ ሰዎች ከሚነሱ ሃሳቦoce ቀድሞ እና ገዝፎ የሚሰማው የሙስና ቅሌቱ በፕሬዚዳንቱ የፓርቲ ፕሬዚዳንትነት ድጋሚ ውድድር አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ነው። የአ,ፍሪቃ ብሔራዊ ኮንግረንስ በመጪው ዓመት ታህሳስ ላይ የፓሪቲውን ሊቀመንበር ያስመርጣል። ለዚያ ነው ነገሮች ከተጠበቁት በላይ እጅጉን ገዝፈው እንዲሰሙ እና እንዲታዩ እያደረገ ያለው ይላሉ ፖለቲካውን የሚተነትኑቱ። 
የሆኖ ሆኖ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎዛ የገቡበት የሙስና ቅሌት በፓርቲያቸው ውስጥ የፈጠረው መከፋፈል ፕሬዚዳንቱን አጣብቂን ውስጥ ከማስገባቱ ባሻገር እስከጣዩ ምርጫ ምን ሊፈጠ,ር እንደሚችል ማንም አስቀድሞ መተንበይ አይቻለውም። 
እንግዲህ ለዕለቱ ያልነውን እና በሁለት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረው የትኩረት በአፍሪቃ ዝግጅታችንም ይኽንኑ ይመስላል። ሳምንት በሌላ ዝግጅት እንጠብቃችኋለን ጤና ይስጥልን።
ታምራት ዲንሳ

Südafrika I Cyril Ramaphos I Untersuchung zu Korruptionsvorwürfen
ምስል Rodger Bosch/AFP

ኂሩት መለሰ