ደቡብ ሱዳን አዲስ ምክትል ፕሬዝደንት መሾሟ፣
ረቡዕ፣ ሐምሌ 20 2008ማስታወቂያ
አምባሳደር ጀምስ ፒቲያ ሞርጋን በሰጡት መግለጫም ግንኙነታቸዉን አቋርጠዋል ያሏቸዉ የምክትል ፕሬዝደንትነት ሥልጣናቸዉን የለቀቁት ሪየክ ማቸርን የደቡብ ሱዳን መንግሥትም ሆነ የራሳቸዉ ፓርቲ ሊያገኛቸዉ ባለመቻሉ በአዲስ ምክትል ፕሬዝደንት እንደተካቸዉ አመልክተዋል። አምባሳደሩ በመግለጫቸዉ አክለዉም ከረዥም ዓመታት ጦርነት እና ትግል በኋላ ራሷን የቻለች ሀገራቸዉ ዉስጥ ለገላጋይነት የሚገባ የዉጭ ኃይል መንግሥታቸዉ እንደማይቀበል አብራርተዋል። መግለጫዉን የተከታተለዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ