1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ ውሳኔ

ረቡዕ፣ መስከረም 5 2014

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚካሂዱት ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን መሰናዶ ማድረጉን የሕዝበ ውሳኔው ማስፈጸሚያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዐስታወቀ። ሕዝቡ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያሳልፍ በክልል መደራጀት በሚኖረው ጥቅምና ጉዳት ዙሪያ እስከ ቀበሌ በሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት መደረጉም ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/40MY0
Äthiopien Hawassa | Mitiku Kedir, Referendum-Projekt
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ከማኅበረሰቡ ጋር እስከ ቀበሌ ውይይት ተደርጓል

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለሚያካሂዱት ሕዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን መሰናዶ ማድረጉን የሕዝበ ውሳኔው ማስፈጸሚያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ዐስታወቀ። ሕዝቡ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲያሳልፉ በክልል መደራጀት በሚኖረው ጥቅምና ጉዳት ዙሪያ እስከ ቀበሌ በሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት መደረጉን የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ምትኩ ከድር ለዶቼ ቬለ (DW) ገልጸዋል። የወሳኔው ውጤት ክልል ሆኖ ለመውጣት የሚያስችለው ከሆነ የሕገ መንግስት ቀረጻ፣ የሥልጣን መዋቅር ድልድል እና ከነባሩ የደቡብ ክልል ጋር የሚኖረውን የሀብትና የዕዳ ክፍፍል የሚያከናውኑ የባለሞያ ቡድኖች (ኮሚቴዎች) ከወዲሁ መዋቀራቸውን ዋና ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።   

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ