1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደምበኞች ቅሬታና የኢትዮ ቴሌኮም ማስጠንቀቂያ

ሐሙስ፣ ጥቅምት 6 2012

ኢትዮ ቴሌኮም ከኩባንያው ፈቃድ ወስደው የተለያዩ አጫጭር መልዕክቶችን ለቴሌኮሙ ደንበኞች ያለ አግባብ እና ያለ ፍላጎታቸው የሚልኩትን እንደማይታገስ አስጠነቀቀ።

https://p.dw.com/p/3RTCz
Der erste Telefonaparat in Äthiopien, Addis Abeba
ምስል DW/Getachew Tedla

የኢትዮ ቴሌኮም ተጠቃሚዎች ቅሬታ

ኢትዮ ቴሌኮም ከኩባንያው ፈቃድ ወስደው የተለያዩ አጫጭር መልዕክቶችን ለቴሌኮሙ ደንበኞች ያለ አግባብ እና ያለ ፍላጎታቸው የሚልኩትን እንደማይታገስ አስጠነቀቀ። ልዩ ልዩ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶችን ከስልክ ደንበኛው ፍላጎት እና ስምምነት በመነሳት የመረጃ ቅብብል እንዲኖር ፈቃድ ቢወስዱም ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ከዚሁ በተቃራኒ ተሰማርተው በመገኘታቸው ፍቃድ የማቋረጥ ርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ኩባንያው ዐስታውቋል። ደንበኞች የማይፈልጉት መልዕክት ወደ ስልካቸው ከመግባቱም ባለፈ ተስማምተው የጀመሩትን የመረጃ ልውውጥ ስምምነት ማቋረጥ እንደሚቸገሩና ገንዘባቸውም ያለ አግባብ እንደማቀነስባቸው ደጋግመው ይናገራሉ። የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰለሞን ሙጬ የቴሌኮም ደንበኞችን አነጋግሮ ቀጣዩን ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል። 
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ