የዩናይትድ ስቴትስና የኢትዮጵያ ግንኙነት
ዓርብ፣ መስከረም 28 2014ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያሳድራል የሚባለዉ ጫና እዚያዉ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና ትዉለደ ኢትዮጵያዉያን ዘንድ ተቃዉሞም ድጋፍም ገጥሞታል።የኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን ሲቢል ምክር ቤት የተባለዉ ማሕበር ሰብሳቢ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ የአሜሪካን መንግስትን ርምጃ እንደሚቃወም ለተለያዩ የሐገሪቱ መስሪያ ቤቶች በፃፈዉ ደብዳቤ አስታዉቋል።የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደምፅ የተሰኘዉ ንቅናቄ ባልደረባ ሜሮን አሐዱም ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የምታደርገዉ ግፊት ለአካባቢዉ መረጋጋት ጠንቅ ነዉ ይላሉ።ጋጤኛ አብረሃ በላይ ግን የዩናይትድ ስቴትስን ርምጃ «ተገቢ»፣ እንዲያዉም «የዘገየ» ብሎታል።
ታሪኩ ኃይሉ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ