የዩናይትድ ስቴት ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 25 2013ማስታወቂያ
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እና የዲዴሞክራቶቹ ተፎካካሪያቸው ጆ ባይደን በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንታዊ ምርጫ እጅግ የተቀራረበ ድምፅ ማግኘታቸው እየተዘገበ ነው። ጆ ባይደን በ50,1 ከመቶ እየመሩ ሲኾን፤ ዶናልድ ትራምፕ ስርጭታችን ከመጀመሩ አንድ ሰአት እስኪቀረው ድረስ 48,3 ድምጽ አግኝተዋል። ይኽ በእንዲህ እንዳለ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከወዲሁ በምርጫው አሸናፊ መኾናቸውን ይፋ አድርገዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች ደጋፊዎች ግጭት ውስጥ የገቡ ሲኾን፤ ፕሬዚደንቱ ይፋዊ መግለጫ ሳይሰጥ አሸነፍኩ ማለታቸው በዩናይትድ ስቴትስ ዴሞክራሲ ላይ ብርቱ ተግዳሮት መደቀኑን ተንታኞች ይናገራሉ። ምርጫውን በተመለከተ የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀን ስቱዲዮ ከመግባታችን አስቀድሞ ቃለ መጠይቅ አድርጌለት ነበር። ምርጫውን እና የአሸነፍኩ አዋጁን ተከትሎ በዩናይትድ ስቴትስ ነዋሪዎች መካከል ስለተፈጠረው ስሜት በመግለጥ ይንደረደራል።
አበበ ፈለቀ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ