የየመን ጦርነት፣ ምክንያትና ዉጤቱ
ሰኞ፣ መጋቢት 20 2013ማስታወቂያ
ሳዑዲ አረቢያ የምትመራዉ የአረብና የአፍሪቃ ተባባሪ ሐገራት ጦር የመንን ከወረረ ባለፈዉ ሳምንት አርብ 6ኛ ዓመቱን ደፍኗል።የሳዑዲ አረቢያ ገዚዎች ያኔ በ6 ሳምንታት ይጠናቀቃል ያሉት ጦርነት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንዳስታወቀዉ ከ230 ሺሕ ህዝብ በላይ ፈጅቷ፤ 4 ሚሊዮን አፈናቅሏል።22 ሚሊዮን ለረሐብና በሽታ አጋልጧል።ጦርነቱ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ።የሳዑዲ አረቢያ ገዢዎች ግን ጦርነቱን በድርድር ለመፍታት እንደሚፈልጉ ባለፈዉ ሳምንት አስታዉቀዋል።የጦርነቱን ምክንያት፣ መዘዙንና የሰላም ጥሪዉን አስመልክተን ከፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲን ጋር ቃለ መጠይቅ አድርገናል።ሙሉዉን ቃለ መጠይቅ ከዚሕ ያድምጡ
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ