ዙማ ፍርድ ቤት ቀረቡ
ዓርብ፣ መጋቢት 28 2010ማስታወቂያ
የቀድሞ የደቡብ አፍሪቃው ፕሬዝዳንት ጄኮቦ ዙማ በቀረበባቸው ክስ ዛሬ ደርባን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው ቃላቸውን ሰጥተዋል። በፓርቲያቸው ግፊት ባለፈው የካቲት ወር ከሥልጣን የወረዱት ዙማ አሁን የቀረበባቸው ክስ በጎርጎሮሳዊው 1990ዎቹ ምክትል ፕሬዝዳንት በነበሩበት ጊዜ ከጦር መሣሪያ ግዥ ጋር በተያያዘ ፈጽመውታል የተባለ የሙስና ወንጀል ነው። የክሱ ጭብጥ ያኔ ደቡብ አፍሪቃ ከአንድ የፈረንሳይ ኩባንያ ጋር በፈፀመችው የ2.5 ቢሊዮን ዶላር የመሣሪያ ግዥ እንዲፈፀም አድርገዋል ፣ ከ24o ሺህ ፓውንድ በላይ ተከፍሏቸዋል የሚል ነበር ። ከዚህ ቀደም የቀረበው ይህ ክስ በጎርጎሮሳዊው 2009 ዓም ለፕሬዝዳንትነት ሲወዳደሩ ውድቅ ተደርጎ ነበር። በቅርቡ አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ክሱ መቋረጡ ትክክል አይደለም ሲል በመወሰኑ ነው ክሱ እንደገና እንዲንቀሳቀስ የተደረገው።
ገበያው ንጉሤ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ