የዘንድሮው ምርጫ በኦሮምያ ክልል
ረቡዕ፣ መጋቢት 22 2013ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልል በስድስተኛ ብሔራዊ ምርጫ ተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች እንደተጠበቀው የነቃ ተሳትፎ አለማድረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ ሊኖረው እንደሚችል ተገለፀ። በተለይም ከምርጫው በኋላ የሚገነባውን መንግሥታዊ እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ተቀባይነት በማጠናከር ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት እንዳይፈትን ያሰጋል ይላሉ አስተያየታቸውን ለዶቼቬለ የሰጡ አንድ የሕግ ባለሙያ፡፡ ከምርጫው መገለላቸውን የሚገልጹት የፖለቲካ ድርጅቶች የፖለቲካ አውድ መጥበብን በዋና ምክንያትነት ሲያቀርቡ መንግሥት በበኩሉ በኢትዮጵያ ከምን ጊዜውም በላቀ አመቺ የፖለቲካ አውድ አለ ሲል ይሞግታል።
ስዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ