1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዕጩ ምዝገባ ተጠናቀቀ

ሐሙስ፣ የካቲት 25 2013

ምርጫ ቦርድ ትናንት እንዳስታወቀዉ ግን እስከ ትናንት ድረስ በምርጫዉ ለመወዳደር ምልክት ከፀደቀላቸው 53 የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ዕጩ ያስመዘገቡት 15ቱ ናቸው

https://p.dw.com/p/3qDba
Äthiopien Birtukan Mideksa UDJ Partei
ምስል Yohannes Geberegziabher/DW

የዕጩዎች ምዝገባ፣ የፖለቲከኞች አስተያየት

 

ኢትዮጵያ ዉስጥ በመጪዉ ግንቦት ማብቂያ በሚደረገዉ ምርጫ የሚወዳደሩ ፖለቲከኞች በዕጩነት የሚመዘገቡበት ጊዜ ዛሬ ተጠናቅቋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣዉ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የዕጩዎች ምዝገባ የተጀመረዉ ባለፈዉ የካቲት 8 ነበር።ምርጫ ቦርድ ትናንት እንዳስታወቀዉ ግን እስከ ትናንት ድረስ በምርጫዉ ለመወዳደር ምልክት ከፀደቀላቸው 53 የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ዕጩ ያስመዘገቡት 15ቱ ናቸው።እስከ ዛሬ የዘለቀዉን ዕጩ የማስዝገብ ሒደትን የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቅሬታም፣ በድጋፍ ደስታም ይገልጡታል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ