የዓይደር ትምሕርት ቤት ድብደባ 22ኛ ዓመት
ዓርብ፣ ግንቦት 28 2012ማስታወቂያ
ኢትዮጵያና ኤርትራ የአንድ ሐገር አንድነታቸዉን አቋርጠዉ እንደ ሁለት ሐገራት መኖር ከጀመሩ ያኔ ገና 7 ዓመታቸዉ ነበር።የአዲስ አበባና የአስመራ አብያተ-መንግሥታትን የተቆጣጠሩት የቀድሞዎቹ አማፂያን ጥብቅ ፍቅር ግን ባድመ ላይ በተፈረጠዉ ጠብ መጎሽ ከጀመረ ወራት ተቆጠሩ።ያም ሆኖ የዚያን ቀን መቀሌ ላይ የሆነዉ ይሆናል ብሎ የጠረጠሩ ከነበሩ እሱ አንድም የአስመራን አዲስ ገዢዎችን ሚንስጥርና አስተሳሰብ በቅርብ የሚያዉቅ አለያም ነብይ መሆን አለበት።ብዙዎቻችን ግን ብዙ ነገር እናዉቅ ነበር።ለምሳሌ ቀኑን።ልክ እንደ ዛሬዉ ሁሉ አርብ ነበር።ዕለቱም ግንቦት 28።ዓመቱ ግን 22 ዓመታት ወደ ኋላ ይተረተራል።1990።የመቀሌ ፀኃይ ጠንከር፣አየሯ ሞቅ ወበቅ ማለት ሲጀምር የዚያች ከዓመታት ጦርነት በቅጡ ያላገገመችዉ ጥታዊ ከተማ ሰማይ አስገመገመ።ዓይደር ትምሕርት ቤት ----ያዩ ያስታዉሳሉ።
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
ነጋሽ መሐመድ
እሸቴ በቀለ