1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዜና

Azeb Tadesse ማክሰኞ፣ ኅዳር 6 2009

https://p.dw.com/p/2SkBh

ኢትዮጵያ ዉስጥ 10 አዉሮጳዉያን አገር ጎብኝዎች ላይ ጥቃት ደረሰ፤ ጎብኝዎቹን የያዘዉን መኪና ሲያሽከረክር የነበረዉ ኢትዮጵያዊ ሾፌር በተተኮሰበት ጥይት መገደሉ ተመልክቶአል።

ዞን ዘጠኝ በሚል ስያሜ ከሚታወቁት የድረ-ገጽ ጸሐፍት መካከል የበፍቃዱ ኃይሉ በድጋሚ መታሰር እንዳሳሰበዉ ድንበር የለሹ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት «RSF» ዛሬ አስታወቀ።   

የጀርመን ፖሊስ  «እራሱን እስላማዊ መንግሥት» ሲል የሚጠራዉን አሸባሪ ቡድን ይረዳሉ የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ የተለያዩ ከተሞችን ማደኑን ገለፀ። የሃገር አስተዳደር ሚኒስትሩ ዛሬ በእስልምና ሥር የሚንቀሳቀስ አንድ ቡድን አግደዋል።  

የአዉሮጳ ጉብኝታቸዉን ዛሬ ከግሪክ የጀመሩት የዩኤስ አሜሪካዉ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ አገራቸዉ ከግሪክ ብሎም ከአዉሮጳ ጋር ያላትን አንድነት ዳግም አረጋገጡ።  ፕሬዚዳንት ኦባማ ነገ ምሽት ላይ ርዕሰ መዲና በርሊን ጀርመን እንደሚደርሱ ይጠበቃል።