1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሶርያ 7.7 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገብቷል

ዓርብ፣ ሰኔ 26 2012

10 አመታት ሊሞላው ወራት በቀሩት የሶርያ የርስ በርስ ጦርነት ከስድስት የአገሪቱ ዜጎች አንዱ ከመኖሪያ ቀዬው ተፈናቅሏል።ባለፈው ማክሰኞ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሶርያውያንን ለማገዝና እንዳልዘነጋቸው ለማስታወስ አንድ ስብሰባ አካሒዷል። በዚሁ ኮንፍረንስ የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት7.7 ቢሊዮን ዶላር ለሶርያ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። 

https://p.dw.com/p/3elEb
Wladimir Putin I Videokonferenz mit Türkei und Iran
ምስል Getty Images/AFP/A. Druzhinin

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለሶርያ 7.7 ቢሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ገባ

በመጪው መጋቢት የሶርያ የርስ በርስ ጦርነት አስር አመታት ይሞሉታል። ደራ በተባለች ከተማ  በትምህርት ቤት ግድግዳ ላይ አብዮታዊ መፈክር የጻፉ ታዳጊዎች ከታሰሩ በኋላ በመንግሥት ላይ የተቀሰቀሰ ተቃውሞ የቀውሱ መነሻ ነበር። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሶርያ ልዩ ልዑክ መረጃ መሠረት ከ400 ሺሕ በላይ ሰዎች በዚህ ጦርነት ተገድለዋል። 
አስር አመታት ሊሞላው ወራት በቀሩት የሶርያ የርስ በርስ ጦርነት ከስድስት የአገሪቱ ዜጎች አንዱ ከመኖሪያ ቀዬው ተፈናቅሏል። ሌሎች 5.5 ሚሊዮን ሶርያውን ደግሞ ከአገራቸው ርቀው በቱርክ፣ ሊባኖስ፣ ኢራቅ፣ እና ግብጽ በዚሁ ጦርነት ምክንያት በስደት ይኖራሉ።ባለፈው ማክሰኞ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሶርያውያንን ለማገዝ እና እንዳልዘነጋቸው ለማስታወስ አንድ ስብሰባ አካሒዷል። በቪዲዮ በተካሔደው በዚሁ ኮንፍረንስ የተለያዩ አገራት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት 6.9 ቢሊዮን ዩሮ ወይም 7.7 ቢሊዮን ዶላር ለሶርያ ለመስጠት ቃል ገብተዋል። 
ገበያው ንጉሴ 

እሸቴ በቀለ