«የፀጥታ ኃይሉ ተመጣጣኝ እርምጃ አለመውሰዱን የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ»ኢሰመኮ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 6 2012ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በቁጥጥር ሥር የዋሉ የዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እስከ ትናንት ድረስ ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ አስታወቀ።ኮሚሽኑ እንዳለው ጉዳዩን በስፍራው ተገኝቶ ለማጣራት እና ለመገምገም መርማሪ ቡድን ለመላክ ዝግጅቱን አጠናቋል።ሆኖም ወደ አካባቢው የሚወስደው መንገድ መዘጋቱ እንቅፋት እንደሆነበት ገልጿል።በሌላ በኩል ዶቼቬለ ያነጋገራቸው የኮሚሽኑ የሃዋሳ ቅርንጫፍ አስተባባሪ በዞኑ የተለያዩ ከተሞች ነሐሴ 4፣2012 ዓም በተከሰቱ ግጭቶች «የፀጥታ ኃይሉ ተመጣጣኝ እርምጃ አለመውሰዱን የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ ብለዋል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ያቀርብልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ