1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዎላይታ ክልል የመመሥረት ጥያቄ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ደረሰ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 17 2012

የዎላይታ ህዝብ ራሱን በቻለ ክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ በአገሪቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አንዲታይለት ጠየቀ ። የዞን ምክር ቤት «ያቀረብኩት ህግ መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ተነፍጎታል» ሲል ዛሬ አቤቱታውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማሰገባቱን የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አበበች ኢራሾ ለዶቼ ቨለ ( DW ) ገልጸዋል ። 

https://p.dw.com/p/3VOnG
Äthiopien | Wolaita Women's March
ምስል Facebook/Author-Wolaita Times

ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከምርጫ ቦርድ በመነጋገር ሕዝበ ውሳኔ እንዲደራጅ ጠይቋል

የዎላይታ ህዝብ ራሱን በቻለ ክልል ለመደራጀት ያቀረበው ጥያቄ በአገሪቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አንዲታይለት ጠየቀ ። የዞን ምክር ቤት «ያቀረብኩት ህግ መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ ተነፍጎታል» ሲል ዛሬ አቤቱታውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማሰገባቱን የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አበበች ኢራሾ ለዶቼ ቨለ ( DW ) ገልጸዋል ። 
 ከዞኑ ምክር ቤት ለቀረበለት በክልል የመደራጀት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም በሚል ወቀሳ እየቀረበበት የሚገኘው የደቡብ ክልል ምክር ቤት እስከአሁን በጉዳዩ ላይ ያለው ነገር ያለም። 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ