1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ወቅታዊ መግለጫ

ሐሙስ፣ ሰኔ 17 2013

የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በፀጥታ ምክንያት እና ሕገ ወጥ ሥራዎችን ይሠራሉ በሚል ኢትዮጵያዊያን ላይ እያደረሰ ያለውን እንግልት ለማስተካከል መንግሥት እየሠራ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ኢትዮጵያውያኑ የመኖሪያ ፈቃድ እያላቸውም እስር፣ እርፊኢ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጠዋል።

https://p.dw.com/p/3vVoF
Äthiopien, Addis Abeba | Ambasador Dina Mufti on press Conference
ምስል Solomon Muchie

«የአየር ጥቃቱ በሕወሓት ታማኝ ታጣቂዎች ላይ ነው የተፈጸመው»፦ መከላከያ

የሳውዲ አረቢያ መንግሥት በፀጥታ ምክንያት እና ሕገ ወጥ ሥራዎችን ይሠራሉ በሚል ኢትዮጵያዊያን ላይ እያደረሰ ያለውን እንግልት ለማስተካከል መንግሥት እየሠራ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ። ኢትዮጵያዊያኑ ችግር ላይ መውደቃቸውን የገለፀው ሚኒስቴሩ በእየ እስር ቤቱ እና በእየ መንደሩ የተጠለሉ ዜጎች መኖራቸው፣ ንብረታቸውም እየተዘረፈባቸው መሆኑን ገልፆ ይህንን ችግር ለመፍታት አንድ ቡድን ተቋቁሞ ከተቻለ በሁለት ሳምንታት ውስጥ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል። ኢትዮጵያውያኑ የመኖሪያ ፈቃድ እያላቸውም እስር፣ እርፊኢ እና እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን በተደጋጋሚ ገልጠዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ስለትግራይ፣ እንዲሁም ስለ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንቅስቃሴ ተናግረዋል። ሩሲያ ኢትዮጵያ ለምታደርገው ማንኛውም የውስጥ ጉዳይ ሥራ ጠንካራ ድጋፍ እንደምታደርግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በኩል ለኢትዮጵያ አቻቸው መናገራቸውን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቃል አቀባይ ኮሎኔል ጌትነት አዳነ፦ ቶጎጋ ውስጥ የተደረገው የአየር ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሳይሆን የሕወሓት ታማኝ ታጣቂዎች ላይ መሆኑን መናገራቸውን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል። 

ሰለሞን ሙጬ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ