1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የጀርመን ቆይታ

ቅዳሜ፣ ኅዳር 19 2013

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ትናንት ተገናኝተው ተነጋግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በተለይም በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለውን ውግያ ለማስረዳት ወደ  ተለያዩ ሀገራት ተጉዘዋል።

https://p.dw.com/p/3lxc2
Äthiopien Addis Abeba  Home grown economic reform Forum | Demeke Mekonnen
ምስል DW/Y. Gebrezihaber

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የጀርመን ጉብኝት እንዴታ?

ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ከጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ትናንት ተገናኝተው ተነጋግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በተለይም የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ከሕወሓት መራሹ የትግራይ ሃይሎች ጋር እየተደረገ ያለውን ውግያ ለማስረዳት ወደ  ተለያዩ ሀገራት ተጉዘዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ  ትናንት እዚህ ጀርመን መጥተው ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሄይኮ ማስ እና ከመራሄተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ዋና አማካሪ ጋር ነው የተወያዩትም የጉዞው አንድ አካል ሆኖ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሄይኮ ማስ በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያ ጦርነቱ እየተካሄደ ባለበት ቦታ ሁሉ የሰብአዊ እርዳታ እንዲደርስ ሁኔታዎችን እንድታመቻች ጠይቀዋል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ታምራት ዲንሳ