1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳምንታዊ መግለጫ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 21 2014

የሰብዓዊ መብት ድጋፍ ያለምንም ገደብ እና መደናቀፍ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። ይሁንና የድጋፍ ሰጪዎች እጥረት እና በመላው ኢትዮጵያ የተረጂዎች ቁጥር መብዛት ሰብዓዊ ድጋፍ በተሟላ ሁኔታ ለማድረስ እክል መፍጠሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/4AdWu
Äthiopien | Pressekonferenz: Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሳምንታዊ መግለጫ

የሰብዓዊ መብት ድጋፍ ያለምንም ገደብ እና መደናቀፍ ወደ ትግራይ ክልል እየገባ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። ይሁንና የድጋፍ ሰጪዎች እጥረት እና በመላው ኢትዮጵያ የተረጂዎች ቁጥር መብዛት ሰብዓዊ ድጋፍ በተሟላ ሁኔታ ለማድረስ እክል መፍጠሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል። ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) አሁን ድረስ በአፋር እና በአማራ ክልሎች በኃይል ከያዛቸው ወረዳዎች አለመውጣቱ የሰብዓዊ ድጋፍ አቅሮቦቱ ላይ ችግር መፍጠሩንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል። በሌላ በኩል ሕወሓት አፋር እና አማራ ክልሎች አሁንም እንደሚገኝ፤ እንደገናም ጦርነት የመቀስቀስ ፍላጎትና ምልክት ማሳየቱንም መንግሥት ዐስታውቋል። የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ሕወሓት አፋር ውስጥ በአራት ወረዳዎች እንደሚገኝ፤ የሕወሓት ተወካይ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡት ሮይተርስ ያደረገው ሙከራ አለመሳካቱንም ትናንት ዘግቦ ነበር።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ