1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች

ማክሰኞ፣ ግንቦት 17 2013

አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ማዕቀብ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥን፣ ቀጣናውንም ችግር ላይ የሚጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገለፀ። ሚኒስቴሩ ርምጃውን የሁለቱን አገራት የመቶ ሀያ ዓመታት ግንኙነት በዜሮ የሚያባዛም ብሎታል።

https://p.dw.com/p/3twAG
Äthiopien Botschafter Dina Mufti
ምስል Press Office Ambassador Dina Mufti

«ማእቀቡ ቀጣናውን ችግር ላይ የሚጥል ነው»

አሜሪካ በኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ላይ የጣለችው የጉዞ ማዕቀብ የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥን፣ ቀጣናውንም ችግር ላይ የሚጥል መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገለፀ። ሚኒስቴሩ ርምጃውን የሁለቱን አገራት የመቶ ሀያ ዓመታት ግንኙነት በዜሮ የሚያባዛም ብሎታል። ይህ ርምጃ ኢትዮጵያ በፀረ አልሸባብ የሽብር ድርጊት መከላከል እና በሰላም ጥበቃ ያላትን ጉልህ ሚና የሚጎዳ መሆኑም ተገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ነገሩን ማጋጋል እንደማትፈልግ ገልፀው ነገር ግን የኢትዮጵያ ነፃነትና ሉዓላዊነት በገንዘብ የማይቀየር ቀይ መሥመር ነው ብለዋል።


ሰለሞን ሙጬ


ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ