የውጭ ጉዳይ ሚንሥቴር መግለጫ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 26 2013ማስታወቂያ
የአውሮጳ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደማይልክ ያሳወቀው ሕብረቱ ያቀረበውን በቅኝ ተገዢ ሀገር እና መንግሥት ካልሆነ በቀር በነፃ ሀገር ሊፈቀድ የማይችል ቅድመ ሁኔታ ኢትዮጵያ ባለመቀበሏ መሆኑ ተገለ። በሕብረቱ የቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚፃረሩ፣ ነፃነቷን የሚዳፈሩ እና ደህነቷን አደጋ ላይ የሚጥሉ መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። የሱዳንን ወቅታዊ አቋም «ቅጥ ያጣ ድፍረት» ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ እስካሁን ያሳየችው ትዕግስት ለመልካም ጉርብትና፣ ለሰላም እና ለቀጣናው ካላት ክብር የመነጨ ነው ብሏል። ሆኖም የሱዳን መንግሥት ኢትዮጵያን በሚመለከት የሚያወጣው መግለጫ ከሰሞኑ የቤኒሻንጉል መሬት የእኔ ነው እስከሚል መለጠጡን አውግዟል።
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ