የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋዜጣዊ መግለጫ
ሐሙስ፣ ጥቅምት 11 2014ማስታወቂያ
መንግሥት በሕገ ወጥ መንገድ በጠብመንጃ ችግር እፈታለሁ ከሚለው ኃይል ውጪ ካሉት ጋር ባዘጋጀው የሰላም ፍኖተ ካርታ ላይ ለመነጋገር በዝግጅት ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል። ይህ የተገለጸው የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው። ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) መቀሌ ከተማ ውስጥ ለጦር መሣሪያ መጋዘን፣ ጥገና እና መስሪያ የሚጠቀምባቸው ቦታዎች ላይ የተፈፀመው የአየር ድብደባ ንፁሃንን ዒላማ እንዳላደረገም በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተጠቅሷል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ በሌሎች ጉዳዮች ላይም ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ