1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና የህዳሴው ግድብ ሙሌት አመለካከት ቀይሯል

ሐሙስ፣ ሐምሌ 15 2013

ኢትዮጵያ ሠላማዊ ሆኖ የተጠናቀቀ ምርጫ ማድረጓ እና የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌትን ማከናወኗ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ ብሎም ሌላው በአገሪቱ ላይ ያለው አመለካከት እንዲቀየር ማድረጉ ተገለፀ።

https://p.dw.com/p/3xsNN
Äthiopien Addis Abeba | Dina Mufti, Sprecher Außenministerium
ምስል Solomon Muchie/DW

«6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እና የህዳሴው ግድብ ሙሌት አመለካከት ቀይሯል»

ኢትዮጵያ ሠላማዊ ሆኖ የተጠናቀቀ ምርጫ ማድረጓ እና የሕዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌትን ማከናወኗ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሁኔታ ብሎም ሌላው በአገሪቱ ላይ ያለው አመለካከት እንዲቀየር ማድረጉ ተገለፀ።
መንግሥት በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፎች በአሮፕላን ጭምር እንዲደርስ ፈቃድ ሰጥቶ ሥራ መጀመሩን የገለፁት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በየብስ በተሽከርካሪ የሚደረገውን ግን የሕወሓት ታጣቂዎች እያስተጓጎሉ መሆኑን ገልፀዋል።
"ሽብርተኛ" ተብሎ የተፈረጀው የሕወሓት ቡድን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔውን አለመቀበሉ እና ጦርነትን መምረጡ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አንድነት እንዲመጡ ማድረግ ማስቻሉን ገልፀው ጉዳዩ አሁን የመላው ኢትዮጵያ ጉዳይ ሆኗል ብለዋል።
በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገር የማስመለሱ ተግባር ተጠናክሮ እስካሁን በተደረጉ 130 በረራዎች 41 ሺህ ዜጎችን መመለስ መቻሉንም ፣ በደቡብ አፍሪካው ሰሞነኛ ቀውስ የሞተ ኢትዮጵያዊ ባይኖርም የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህክምና ላይ የሚገኙ መኖራቸውን ቃል ዐቀባዩ ተናግረዋል።

ሰሎሞን ሙጬ

ታምራት ዲንሳ 

ኂሩት መለሰ