1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማብራሪያ በተወካዮች ምክር ቤት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 9 2014

ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጣዊ እና ውጫዊ ፈተናዎች በርትተውባት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጫና ማስተናገዷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። የዘርፉ ሥራዎች በእጅጉ ፈተና የበዛባቸው ሆነው መቀጠላቸው አይቀሬ መሆኑንም ምክትልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4BPeT
Äthiopien Parlament Addis Abeba
ምስል Solomon Muche/DW

ውስጣዊ እና ውጫዊ ብርቱ ፈተናዎች

ኢትዮጵያ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጣዊ እና ውጫዊ ፈተናዎች በርትተውባት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ጫና ማስተናገዷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናገረ። የዘርፉ ሥራዎች በእጅጉ ፈተና የበዛባቸው ሆነው መቀጠላቸው አይቀሬ መሆኑንም ምክትልና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት እና በቀጠናው ስላላት ግንኙነት ማብራሪያ ተሰጥቷል። ከቱርክ ጋር የተደረገው የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት እንዲሁም የአንድ መቶ ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ የወታደራዊ የገንዘብ ድጋፍ ትብብር ስምምነት መጽደቁም ተነግሯል።

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከጎረቤት አገራት ጋር ጥሩ የሚባል ግንኙነት ማሳለፏም ተገልጿል። ይሁንና ሱዳን ኢትዮጵያ ላይ አደገኛ ውጤት የሚያስከትል የተባለ ወረራ መፈጸሟ ተገልጿል። ከኤርትራ ጋር ያላት ግንኙነትም ሕጋዊ ማዕቀፍ ኖሮት ተቋማዊ አለመሆኑ ጥያቄ አስነስቷል። 

ምክትልና የውጭ ገዳይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት የዘጠኝ ወራት የሥራ ዘገባ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የምዕራቡ ዓለም አገራትና ድርጅቶች የሰብዓዊ መብትን ጉዳይ እንደ የፖለቲካ መሣሪያ በመጠቀም ጫና ማድረጋቸው ተጠቅሷል። 

ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ በተለይ በቀይ ባሕር ቀጣና ተመልካች ከመሆን ወጥታ የወሳኝነት እና የተሰሚነት ደረጃዋ እንዲያድግ መንግሥት ትኩረት መያዙም ተነግራል። 
ኢትዮጵያ ከአሜሪካ የባይደን አስተዳደር ጋር ሻክሮ የሚገኘው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ መሻሻል እያሳየ ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ላይ አደገኛ ጉዳት ያስከትላሉ የተባሉት ረቂቅ የማዕቀብ ሕግጋት እንዳይጸድቁ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ለምክር ቤቱ አስረድተዋል። 

በተጨማሪም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ እና በቱርክ መንግስታት መካከል ነሐሴ 12 ቀን፣2013 ዓ.ም አንካራ ላይ የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት እንዲሁም የአንድ መቶ ሚሊዮን የቱርክ ሊሬ የወታደራዊ የገንዘብ ድጋፍ ትብብር ስምምነት አጽድቋል።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ኂሩት መለሰ