የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 13 2013ማስታወቂያ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ታይፕ ኤርዶጋን ጋር በውኃ ልማትና መከላከያ ዘርፎች ላይ ስምምነት መፈራረማቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ቱርክ በኢትዮጵያ ውስጥ ከቻይና ቀጥላ ሰፊ የንግድና የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት ተሳትፎ ያላት አገር በመሆኗ ጉብኝቱ ይህንንም ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚያግዝም አመልክቷ። በዛሬው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሳምንታዊ መግለጫ የአሜሪካ የምሥራቅ አፍሪካ ልዩ መልዕክተኛ የኢትዮጵያን ቆይታ፤ ከሳውድ አረቢያ ስለሚመለሱ ዜጎች ጉዳይ፤ ስለሚዘጉ ቆንስላ ጽሕፈት ቤቶች እና ተያያዥ ጉዳዮች ማብራሪያ ተሰጥቷል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ