1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ

ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2011

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሃገራት ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዜጋ ተኮር አሠራርን የተመለከተ መግለጫ በዛሬው ዕለት ሰጠ። ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ስለታሠሩት ኢትዮጵያንም እንዲሁ አስፈላጊው ክትትል እየተደረገ መሆኑም ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/3NfAY
Äthiopien Nebiat Getachew Sprecher im Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውንን ይመለከታል

 የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ  ለሥራ ወደ ውጭ የሚሄዱ ኢትዮጵያውያንን  የደሞዝ አከፋፈል እንዲሁም ሠራተኞችን በሕጋዊ መንገድ ስለመላክ፤ ስደተኞችን ወደ ሀገር መመለስን በሚመለከት ስላለው ዲፕሎማሲያዊ አሠራር አብራርተዋል። አዲሱ የሥራ ፈቃድ ውል ስራ ላይ ከዋለ ወዲህ የተገልጋዩ ቁጥር እጅግ  በመጨመሩ ተገቢውን የሰነድ ማረጋገጥ ሥራ የሚያከናውነው አካል እጅግ በርካታ ሰዎችን በየቀኑ እያስተናደ መሆኑንም አመልክተዋል።   መግለጫውን የተከታተለው ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

 ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ