1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ መግለጫ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ

ሐሙስ፣ መጋቢት 8 2014

በሳውዲ አረቢያ በእሥር እና በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ሰላሳ አምስት ሺህ ያህሉ ወደ አገራቸው ለመመለስ መመዝገባቸው ተገለፀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው 100 ሺህ ዜጎችን ከሳውዲ ለምምለስ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በእሥር ላይ የሚገኙም ሆነ በውጪ ያሉት እንዲመለሱ ይደረጋል።

https://p.dw.com/p/48dpk
Saudi Arabien Riad Unruhen
ምስል AFP/Getty Images

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል

በሳውዲ አረቢያ በእሥር እና በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል ሰላሳ አምስት ሺህ ያህሉ ወደ አገራቸው ለመመለስ መመዝገባቸው ተገለፀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው 100 ሺህ ዜጎችን ከሳውዲ ለምምለስ በተያዘው ዕቅድ መሠረት በእሥር ላይ የሚገኙም ሆነ በውጪ ያሉት እንዲመለሱ ይደረጋል። የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በዛሬው መግለጫቸው የዓለም ጤና ድርጅት በትግራይ ስላለው የጤና አገልግሎት ችግር መናገራቸው ተጠቅሶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ዳይሬክተሩ ችግሩ በአማራም፣ በአፋርም መኖሩን ቢናገሩ ካሉ በኋላ ለይቶ ማልቀስ እና ማዘን ተገቢ አይደለም ብለዋል። ኢትዮጵያ አውዳሚ ጦርነት ውስጥ የገቡት ሩሲያ እና ዩክሬን ድጋፍ ለማሰባሰብ በሚያደርጉት ጥረት ገለልተኛ አቋም ስለመያዟ እና ሁለቱ አገሮች ልዩነታቸውን በሰላማዊ መንገድ ቢፈቱ ይሻላል፣ ለዓለምም የሚበጀው ይህ ነው በሚል አቋሟን በተባበሩት መንግሥታት ውስጥ ግልጽ ማድረጓ በመግለጫው ተጠቅሷል። 

ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ