የውጭ ንግድ የገጠመው ችግር
ሰኞ፣ ጥቅምት 10 2012ማስታወቂያ
ዶላርን በመፈለግ ሰበብ በውጭ ንግድ ውስጥ መግባት፣ የሀገር ውስጥ ምርቶችን ዋጋ ከዓለም አቀፍ ዋጋ እጅግ አሳንሶ መላክ፣ የኮንትራት ክህደት መፈጸምና የውጭ ምርቶችን ደብቆ ለሀገር ውስጥ ገበያ ማቅረብ፤ ዋና ችግሮች መሆናቸውን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምሥጋኑ አረጋ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል።
ይህም በመሆኑ ከተለያዩ ሃገራት በኢትዮጵያዊ ላኪዎች የውል ክህደት ተፈጸመብን የሚሉ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች የንግድ አጋሮች ለኢትዮጵያ መንግሥት እንደመጣም ተናግረዋል። ይህንን የዘርፉን ሥራ እንዲያሽቆለቁል ያደረገውን ችግር ለመፍታት ላኪዎች በውል መሠረት፣ በተጠያቂነትና በፍትሃዊነት ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የሚያስገድድ አዲስ የኮንትራት አስተዳደር ሥርአት መዘርጋቱንም አብራርተዋል። ከአዲስ አበባ ዝርዝር ዘገባ ደርሶናል።
ሰለሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ተስፋለም ወልደየስ