የውይይት መድረክ በዋልታ ኢንፎርሜሽን
ሐሙስ፣ ኅዳር 4 2012ማስታወቂያ
ጋዜጠኞች የሀገር ህልውና በማስቀጠል እና የተረጋጋ ሰላም በማምጣት ረገድ የበኩላቸውን ሚና መጫወት እንዳለባቸው ተገለጸ። ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና መጪውን ምርጫ በተመለከተ በዛሬው ዕለት ባዘጋጀው መድረክ ጋዜጠኞችን፣ የፖለቲካ አራማጆችን እና ፖለቲከኞችን አወያይቷል። መድረኩ ከተዘጋጀባቸው ምክንያቶች አንዱም የሃሳብ ልዩነቶችን በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ ማውራት ተገቢ መሆኑን ለማሳየት መሆኑ ተገልጿል። ከአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝሩን ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ