1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዋሊያዎቹ የመጨረሻ ጭላንጭል ተስፋ

ዓርብ፣ ጥር 6 2014

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ትናንት ከካሜሩን ጋር ባደረገው ግጥሚያ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል። በተለይ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ድንቅ ጨዋታ ያሳዩት ዋሊያዎቹ በካሜሩን 4 ለ1 ነው የተሸነፉት። ሦስተኛ ጥሩ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድል አለው። ዋሊያዎቹ ቀጣይ ግጥሚያቸው ከቡርኪና ፋሶ ጋር ነው።

https://p.dw.com/p/45Y8o
Fußball Afrika-Cup 2022 I Kamerun vs Äthiopien
ምስል Kenzo Tribouillard/AFP

ቀጣዩ ግጥሚያ ከቡርኪና ፋሶ ጋር ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ትናንት ከካሜሩን ጋር ባደረገው ግጥሚያ ሁለተኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል። በተለይ የመጀመሪያው አጋማሽ ላይ ድንቅ ጨዋታ ያሳዩት ዋሊያዎቹ በካሜሩን 4 ለ1 ነው የተሸነፉት። ሦስተኛ ጥሩ ቡድን ወደ ቀጣዩ ዙር የማለፍ ዕድል አለው፤ ዋሊያዎቹ በርካታ የግብ እዳ አለባቸው። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ትናንት በካሜሩን መሸነፉ ለአፍሪቃ ዋንጫ ቀጣይ ዙር የነበረውን ዕድል እጅግ አጠበበ። ምንም እንኳን እጅግ ውብ ጨዋታ ቢያሳይም የኢትዮጵያ ብሔራዎ የእግር ኳስ ቡድን ትናንት ለአፍሪቃ ዋንጫ የዙር ውድድር ባደረገው ሁለተኛ ግጥሚያ በአዘጋጇ ካሜሩን ቡድን 4 ለ1 ተሸንፏል። የካሜሩን ቡድን በርካታ ተጨዋቾች በተለያዩ ታላላቅ የአውሮጳ ሊግ ቡድኖች ውስጥ የሚጫወቱ ታዋቂ ተጨዋቾች ናቸው። ቀጣዩ ግጥሚያ ከሌላኛዋ የምድቡ ብርቱ ፎካካሪ ቡርኪና ፋሶ ጋር ነው። ስለትናንቱ ጨዋታ እና ስለዋሊያዎቹ የመጨረሻ ተስፋ የሶከር ኢትዮጵያ ድረ ገጽ አዘጋጅ ሚካኤል ለገሰ ከዶይቸ ቬለ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል።  

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ