1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ

ሐሙስ፣ መጋቢት 15 2014

የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ  ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  "የዳቦ ስም የተሰጣቸው" ያሏቸው ረቂቅ ሕግጋት የኢትዮጵያ መንግሥት ደካማና የሚጠመዘዝ መንግሥት እንዲሆን የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል

https://p.dw.com/p/48zuP
Amabassdor Dina Mufti (Ministry of Ethiopian foreign affairs spokesperson)
ምስል Solomon Muche/DW

«ረቂቅ ሕግጋቱ ከፀደቁ የሁለቱ ሐገራት ነባር ግንኙነት ይበላሻል» ኢትዮጵያ

የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያና መወሰኛ ምክር ቤቶች ያረቀቋቸዉ ኢትዮጵያን የሚመለከቱ ሁለት ሕግጋትን የኢትዮጵያ መንግሥት አጥብቆ እንደሚቃወማቸዉ  በአፍሪቃ ቀንድ ለዩናይትድ ስቴትስ  ልዩ መልዕክተኛ መናገሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።የሚኒስቴሩ ቃል ዐቀባይ  ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ  "የዳቦ ስም የተሰጣቸው" ያሏቸው ረቂቅ ሕግጋት የኢትዮጵያ መንግሥት ደካማና የሚጠመዘዝ መንግሥት እንዲሆን የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።HR6600 እና S.3199 የተባሉት ረቂቅ ሕግጋት ከፀደቁ የሁለቱን ሐገራት ታሪካዊ ግንኙነት ክፉኛ ይጎዳሉ ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ለልዩ መልእክተኛው መናገራቸው አምባሳደር ዲና አስታዉቀዋል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ