1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ መዘግየት የፈጠረው ቅሬታ እና የቆራሪት ከተማ ውዝግብ

ረቡዕ፣ ግንቦት 26 2012

በትግራይ ክልል በወልቃይት ወረዳ ቆራሪት በተባለ ቦታ የተሰባሰቡ ገበሬዎች የመንደራቸው አስተዳደራዊ መዋቅር በከንቲባ የሚመራ ከተማ እንድትሆን መወሰኑ ተቃውሞ ገጥሞታል። የአካባቢው ገበሬዎች ቅሬታ የፈጠረባቸው ግን የቆራሪት መንደር ወደ ከተማ አስተዳደር መቀየሯ ብቻ አይደለም። በወልቃይት ይገነባል የተባለ የስኳር ፋብሪካ መዘግየት ሌላው ጉዳይ ነው

https://p.dw.com/p/3dDIr
Zucker
ምስል bit24 - Fotolia

የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ መዘግየት የፈጠረው ቅሬታ እና የቆራሪት ከተማ ውዝግብ

በትግራይ ክልል  በምዕራባዊ ዞን ወልቃይት ወረዳ  ቆራሪት በተባለ ቦታ የተሰባሰቡ ገበሬዎች የመንደራቸው አስተዳደራዊ መዋቅር በከንቲባ የሚመራ ከተማ እንድትሆን መወሰኑ ተቃውሞ ገጥሞታል። በገጠር አስተዳደራዊ መዋቅር እንዲቆይ የሚሹ ነዋሪዎች ወደ ሽረ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚወስደው መንገድ እስከ መዝጋት ደርሶ ነበር።

የአካባቢው ገበሬዎች ቅሬታ የፈጠረባቸው ግን የቆራሪት መንደር ወደ ከተማ አስተዳደር መቀየሯ ብቻ አይደለም። በወልቃይት ይገነባል የተባለ የስኳር ፋብሪካ መዘግየት ቅሬታ አሳድሮባቸዋል።

የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ በአመት 4 ሚሊዮን 840 ሺ ኩንታል ስኳር እና 41 ሚሊዮን 654 ሊትር ኢታኖል ያመርታል ተብሎ ታቅዶ እንደነበር የስኳር ኮርፖሬሽን መረጃ ይጠቁማል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

እሸቴ በቀለ