የካሾጂ ግድያ፣ የአሜሪካኖች ዘገባና ሳዑዲ አረቢያ
ሰኞ፣ የካቲት 22 2013ማስታወቂያ
ሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት መጠናቀቂያዉ ነዉ።ጦርነቱ ያነደደዉ ዓለም ግን ለቀዝቃዛዉ ጦርነት ዉሽንፍር እየሰነቀ ነዉ።ዕለቱ፣ በተለይ ለአዉሮጳ-አሜሪካኖች የፍቅር ቀን ነዉ።የካቲት 14፣ 1945 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሪያኑ አቆጣጠር ነዉ።) የበረሐማዋ ግን ስልታዊቱ ሰፊ፣ የነዳጅ ቋት ሐገር ንጉስና የሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት አሸናፊ፣ ኃያል፣ ሐብታም ሐገር ፕሬዝደንት በዚያ የጦርነት ፍፃሜ ግን የአዲስ ቀዝቃዛ ጦርነት ዋዜማ፣ በዚያች የፍቅር ቀን፣ አል ቡሐይራሕ አል-ሙራ አል ኩብራ-በተባለዉ የግብፅ ጨዋማ ሐይቅ ላይ የሁለቱን ሐገራት ፖለቲካዊ ጋብቻ ፈጠሙ።የጋዜጠኛ ጀማል ኻሾጂ ግድያ ቅሌት የ76 ዘመኑን ጋብቻ ያፈርሰዉ ይሆን? ከፖለቲካ ተንታኝ የሱፍ ያሲን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
ነጋሽ መሐመድ