1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች አቤቱታ

ረቡዕ፣ ጥር 12 2013

ነዋሪዎቹ በሰገን ዙሪያ ወረዳ የተነሳ ግጭት በመሸሽ በደራሼ ልዩ ወረዳ ቢጠለሉም አስከአሁን ድጋፍ አንዳልቀረበላቸው ገልጸዋል። በተጠለሉበት ስፍራ በመገኘት ያናገሯቸው የክልሉ ባለስልጣናት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ወደ ቀያቸው ሲመለሱ እንደሚያገኙ ነግረውናል የሚሉት ተፈናቃዮቹ ባለው የጸጥታ ስጋት የተነሳ ጥያቄውን ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ተናግረዋል

https://p.dw.com/p/3oAYS
Äthiopien Konflikt zwischen Konso & Ale
ምስል Ale Communication Office

የኮንሶ ዞን ተፈናቃዮች አቤቱታ

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን <<ልዩ ወረዳ እንመሰርታለን >> በሚሉና ጥያቄውን በሚቃወሙ ቡድኖች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ባለማግኘታቸው መቸገራቸውን እየተናገሩ ይገኛሉ።
ነዋሪዎቹ ባለፈው ሳምንት በዞኑ ሰገን ዙሪያ ወረዳ የተነሳውን ግጭት በመሸሽ ወደ ደራሼ ልዩ ወረዳ ገብተው ቢጠለሉም አስከአሁን ምግብና መጠለያ ጨምሮ የእለት ደራሽ ድጋፍ አንዳልቀረበላቸው ገልጸዋል።
በተጠለሉበት ስፍራ በመገኘት ያናገሯቸው የክልሉ ባለስልጣናት የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ወደ ቀያቸው ሲመለሱ እንደሚያገኙ ነግረውናል የሚሉት ተፈናቃዮቹ ባለው የጸጥታ ስጋት የተነሳ ጥያቄውን ሳይቀበሉት መቅረታቸውን ተናግረዋል።
የክልሉ ባለስልጣናት በበኩላቸው በዞኑ ግጭቱን የቆሰቆሱና የተሳተፉ ቡድኖች በህግ ጥላ ስር እየዋሉ ፣ አካባቢውም እየተረጋጋ ይገኛሉ ብለዋል ።

ሸዋንዛው ወጋየሁ 
ሸዋዬ ለገሠ